Get Adobe Flash player

ወገራ ወረዳ

የወገራ ወረዳ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጎንደር መስተዳደር ዞን ውስጥ  የምትገኝ ወረዳ ስትሆን የወረዳዋ ዋና ከተማ አምባ ጊዮርጊስ የሰሜን ጎንደር ዋና ከተማ ከሆነችው ከጎንደር ከተማ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሰሜን በኩል ትገኛለች ፡፡

ወረዳዋ ከ1985 ዓ.ም በፊት በዳባት አውራጃ ስር የነበረች ሲሆን ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ራሷን  ችላ ተቋቁማለች ፡፡ የወገራ ወረዳ ከባህር ወለል በላይ  ከ1500-3020 ሜትር በሚደርስ ከፍታ የምትገኝ ሲሆን ከ400-600ሚሊ ሊትር አመታዊ የህዝብ መጠን ታገኛለች ፡፡የሙቀት መጠኗን ስንመከት ደግሞ ከ18-37 ድግሪ ሴልሽስ እንደሚሆን መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡ወረዳዋ በ41 ቀበሌዎች የተከፋፈለች ሲሆን ሁለቱ የከተማ ቀበሌዎች 39ኙ ደግሞ የገጠር ቀበለዎች ከዚህም ውስጥ 20ዎቹ ደጋማ /ሁለቱን የከተማ ቀበሌዎች ጨምሮ / 15ቱ ቆላማ ቀበሌዎች 6ቱ በምዕብ የወረዳዋ ክፍልና 9ኙ በምስራቅ የወረዳዋ ክፍል የሚገኙ ናቸው ፡፡እና ቀሪዎቹ 6ቱ ቀበሌዎች በወይና ደጋ ስር የሚገኙ ቀበሌዎች ናቸው ፡፡በወረዳዋ በምስራቅ በኩል የሚገኙ 9 ቀበሌዎቸችና ከደጋዎቹ 7ቱ ቀበሌዎች በጥቅሉ 16ቱ ቀበለዎች ዝናብ አጠር ቀበሌዎች በመሆናቸው ሴፍትኔት የታቀፉ ቀበሌዎች ናችው ፡፡

የአየር ንብረት

Ø 44%------------------------ደጋማ

Ø 33%---------------------- ወይና ደጋ

Ø 23%----------------------- ቆላማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በወረዳዋ በዋናነት የሚበቅሉትን አዝርዕቶች ስንመለከት ገብስ /የምግብና የቢራ/ ስንዴ፤ጤፍ፤ ማሽላ ፤ዳጉሳ፤ በቆሎ፤ አብሽ፤ ምስር፤ አተር፤ ባቄላ፤ ሽምብራ፤ ተልባ፤ ሰለጥ፤ ጓያ፤ሲሆኑ/ የወረዳዋን  የቤት እንስሳት ሀብት ስንመለከት በሬ፤ላም፤አህያ፤ፈረስ፤በቅሎ፤ፍየል ፤በግ፤በስፋት በወረዳዋ ይገኛሉ ፡፡

የአፈር አይነት

Ø 30%----------------------ጥቁር አፈር

Ø 15%---------------------ግራጫ አፈር

Ø 15%--------------------ቡናማ አፈር

Ø 40%-------------------- ሌሎች አፈር ይዞታችን ያካትታል ፡፡

የወረዳዋ አዋሳኞች

v በሰሜን የዳባት ወረዳ

v በሰሜናዊ ምስራቅ የጃናሞራ ወረዳ

v በምስራቅ የምስራቅ በለሳ ወረዳ

v በደቡብ የምዕራብ በለሳና የጎንደር ዙሪያ ወረዳ

v በምዕራብ የታች አርማጭሆና የላይ አርማሆ ወረዳዎች ያዋስኗታል ፡

የወረዳዋ የመሬት አቀማመጥ ና የህዝብ ብዛት

በወረዳዋ 182131.786 ሄ/ር /186፣250ካሬ ኪ.ሜተር /የቆዳ ስፋት ያላት ሲሆን ፡-

* 50% 91,065.893 ሄ/ር------------------------------ሜዳማ

* 15% 27,319.786 ሄ/ር---------------------------- ወጣ ገባ

* 25% 45,532.946 ሄ/ር-----------------------------ተራራማ

* 10%18,213.178 ሄ/ር ----------------------------- ሸለቋማ ና ሌሎች ሰብሎች የወረዳዋ  የመሬት ገፅታ ናቸው፡፡

በወረዳዋ የሚኖረው የህዝብ ብዛት 277,946 ሲሆን የቨውም

* በከተማ ወንድ =7,671 ሴት = 10,095 ድ =17,766

* በገጠር ወንድ 134,233 ሴት =125,947 ድ =260,180 ሲሆን የህዝቡን የመተዳደሪያ ሁኔታ ስንመለለከት ደግሞ 98% በእርሻ ክፍል ኢኮኖሚ የሚተዳደር ሲሆን ቀሪውና ሁለት ፐርሰንቱ ደግሞ በንግድና እደ ጥበብ ስራዎች የሚተዳደር ነው ፡፡

የልዪ ትም/ት መስጫ ት/ቤት

አንድ ያላት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ከዘጠና በላይ የሚሆኑ የሳተላይት ክፍሎች ም ይገኛሉ ፡፡በወረዳዋ ዋና ከተማ በሆነችው በአምባጊዎርጊስ ከተማ ደግማ አንድ የመሰናዶ ት/ቤት ይገኛል፡፡

የሰርቲፊኬት መምህራን

ü ወንድ =253 ሴት 467 ድምር 720

የዲፕሎማ መምህራን

ü ወንድ =202 ሴት =165 ድምር 367

የዲግሪ መምራን

ü ወንድ =69 ሴት =20 ድምር =89 በድምሩ 524 ወንድና 652 ሴት መምራን ተሰማርተው ይገኛሉ ፡፡

የመንግስት የጤና ተቋማት

· ጤና ኬላ =26

· ጤና ጣቢያ =10 ከዚህ ውስጥ 8ቱ ሙሉ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆኑ ሁለት ደግሞ በቅርቡ አገልግሎቱን የሚጀምሩ ናቸው

የግል የጤና ተቋማት

· ፋርማሲ = 4

በወረዳዋ የሚገኙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ተቋማት ግብርናና ገጠር ልማት

የተለያዪ ቴክኖሎጅዎችን ወደ አርሶ አደሩ ለማድረስና ለማላመድ በዚህም የአርሶ አደሩን ንቁ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በወረዳዋ ፡-

ü በ33 ቀበሌዎች አገልግሎት የሚሰጡ

ትምህርት

v አማራጭ ትም/ት ቤት =24

v ከ1-4 ክፍል ትም/ት ቤት =27

v ከ5-8ኛ ክፍል ትም/ት ቤት=52

v ከ9-10 ክፍል ትም/ት ቤት =2

v አፀደ ህፃናት ትም/ቤት =1

ወጣቶች ስፖርት

በወረዳዋ ዋና ከተማ በአምባጊወርጊስ ከተማ አንድ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ከ198,000 በላይ ብር ተገንብቶ አገልግሎት ለመስጠት በዝግጅት ላይ ሲሆን

ማዕከሉ በውስጡም ፡-

v የቤቶች ውስጥ መዋጮ

v ካፍቴሪያ

v የመረጃ ማዕከል

v የኪነት ቡድኖች  የመልበሻ ክፍልና በአንድ ጊዜ ከ300 በላይ ሰዎች ማስተናገድ የሚችል አደራሽ አለው ፡፡

ጥቃቅንና አነስተና ንግድ ስራዎች ማስፋፊያ

በወረዳዋ ዋና ከተማ አንድ የማህበረሰብ ክህሎት ስልጠና ማዕከል ይገኛል ይህ ማዕከል በተለያዪ ጊዜያት የተለያዪ ስራ አጥ ወጣቶችና በዝቅተኛ የንሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዪ የስራ መስኮች በማሰልጠን ወደ ስራ እያሰማራን ይገኛል

በወረዳዋ የሚገኙ የተለያዪ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ና ፕሮጀክቶች እንቅስቃሴ

መንገድ ፡-

በወረዳችን የመንገድ ተጠቃሚነት ስናይ ከጎንደር ደባርቅ የሚወስደው መንገድ ወረዳዋን ለሁለት ከፍሎ በአ/ጊስ ከተማና በገደብጌ ከተማ አድርጎ የሚያልፍ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በወረዳዋ የሚገኘውን ህብረተሰብ እርስ በእርስ ለማግኘትና ጥሩ የሆነ የገቢያ ትስስር እንዲኖር ለማድረግ እንዲሁም ወደ ከተማ ለመለወጥ የሚፈጀው ረጅም ሰዓትና ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በምስራቁ የወረዳችን ክፍል 5 ቀበሌዎችን በመሀል በመሰንጠቅ /በመክፈል/ ስላሬ የገቢያ ማዕከል የሚያደርስ 50 ኪ.ሜ መንገድ ተሰርቶ ሚያዚያ 2000 ዓ.ም ለምርቃት በቅቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ሌላው በወረዳችን በምዕራቡ በኩል የሚገኙ ቆላማ ቀበሌዎችን እርስ በእርስ ና ከከተማ ጋር ለማገናኘት 2ቀበሌዎችን  በመሀል በመክፈል መረባ ድረስ 32 ኪ.ሜ ማዕከሉ ላይ  የሚያደርስ 50 ኪ.ሜ መንገድ ተሰርቶ ሚያዚያ 2000ዓ.ም ለምርቃት በቅቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ፡፡ኪዚህ በተጨማሪ በወዳዋ ቀበሌን ከከበሌ እና ቀበሌን ከከተማ የሚያገናኙ የተለያዪ አቅጣጫዎች በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ በርካታ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችም ይገኛሉ፡፡

የመሰረተ ልማት አውታሮቸ

መብራት :-የወረዳዋ ዋና ከተማና ንዑስ ከተማ እስከ 1993 የመብራት ተጠቃሚ ያልሆኑበት ጊዜ ሲሆን ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ግን ሁለቱም ከተሞች የጀኔሬት መብራት ተጠቃሚ ሆነው ቆይተዋል

ስለዚህ መንግስት ይህንን የህዝብ ጥያቄና ፍላጎት ለማርካትና የህብረተሰቡን የመብራት ተጠቃሚነት ለማሳደግ ሁለቱም ከተሞች ከ1995 ጀምሮ የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በገጠሩ የወረዳዋ ክፍል በአንድ ቀበሌ የሙሉ አግልግሎት ጠጠቃሚ ሲሆን በሁለት ቀበለዎች የመስመር ዝርጋታ ስራ እየተራ ይገኛል ፡፡

ስልክ ፡- በወረዳዋ ዋና ከተማና ንዑስ ከተማ ከ -------------ዓ.ም ጀምሮ እስከ ---- ዓ/ም የተዘዋዋሪ ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑበት ጊዜ ነበር በአሁኑ ወቅት በሁለቱም ከተሞች ያሉ ተጠቃሚዎች ብዛት 574 ያህል ደርሷል ::

ከዚህ በተጨማሪ ወረዳዋ የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ ለማድረግ የማይክሮ ዌብ ተከላ ተካሂዶ አገልግሎት ጀምሮአል ፡፡ በዚህም የማክሮ ዌብ አማካኝነት ከ2 የከተማ ቀበሌዎች በተጨማሪ የወረዳዋ- የገጠር ቀበሌዎች  የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ ሁነዋል ፡፡በ1999 ዓም ጀምሮ ወረዳዋ ቋሚ የፖስታ አገልግሎት ጨምሮ የተለያዪ አገልግሎቶች ለህ/ሰቡ እየሰጠ ይገኛል የተራ ሃዋላ አግልግሎት ጨምሮ የተለያዪ አገልግለቶችን ለህ/ሰቡ እየሰጠ ይገኛል ፡፡

ዘላቂ ተፈጥሮ ሀብት ልማት ፕሮግራም

ውሃ ፡-በወረዳችን የንፁህ መጠጥ ውሃን ስንመለከት በወረዳዋ ባሉ39 የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በ33 ያህሉ ቀበሌዎች ከ182 በላይ የንፁህ ውሃ አቅርቦቶች ለህ/ሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡

በዚህም በወረዳዋ የገጠር ቀበሌዎች ከሚኖረው ህዝብ መካከል 57,847 ያህሉ የንፁህ ውሃ መጠጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በወረዳዋ ባሉ ቀበለዎች 60 ያህል ግንባታዎችን ለማከናዎን እንቅስቃሴ ተጀምሯል ፡፡ ወደ ከተማ ቀበሌዎችን ስንመጣ ደግሞ በሁለቱም ቀበሌዎች ከ1987 ዐ.ም በፊት የመጠጥ ውሃ የሚያገኘው ከምንጭ ሲሆን ይህ ውሃ አቅርቦት ለተለየዪ ውሃ ወለድ በሽታዎች የሚያጋለጥ ከመሆኑም ባሻገር ለመምጣትም ርቀት ያለው መንግድን መጓዝ ግድ ስለሚል አድካሚ ነበር ፡፡በመሆኑም ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ቡለቱም ከተሞች የሚኖረው ህዝብ የንፁህ ውሃ መጠጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ከ20,000እስከ 64,000ሊትር መያዝ በሚችሉ ማጠራቀሚያ ንህፅህናው የጠበቀ ውሃ በማጠራቀም ንህዝቡ በየቤቱና በቦኖ ተጠቃሚ እንዲሆን ሆነዋል ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የገጠሩ ህዝብ የላቀ የንፁህ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በወረዳዋ ባሉ ቀበሌዎች 60 ያህል ግንባታዎች ለማከናዎን እንቅስቃሴ ተጀምሯል ፡፡

የወረዳዋ የመስህብ ሀብቶች

ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት

የጩጊ ማርያም ገዳምና የአባ ምዕመነ ድንግል ዋሻ

በወረዳዋ ዋና ከተማ ከአንባጊዎርጊስ ከተማ በምዕራብ በኩል በ10ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ወይንም ከጥንታዊቷ የጎንደር ከተማ ወደ ሰሜን /ደባርቅ/ በሚወስደው ዋናው መንግድ በ30 ኪ.ሜትር ላይ የኮሶየ አምባራስ ቀበሌን እናገኛለን ፡፡ የኮሶየ ቀበሌ ከባህር ወለል በላይ በ3000 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ የኮሶየ ዛፍን በብዛት የምታበቅል በመሆኗ ኮሶየ እንደተባለ ች በካባቢው የሚኖሪ ቀደምት አባቶችና አፈታሪኮች ያስረዳሉ ፡፡የቀበሌዋ ሰሜናዊ ምዕራብ  ክፍል ለአይን በሚማርኩ ተራሮች ሸለቆዎች ሸንተረሮችና በተለያዪ ተፈጥሮአዊ ደኖች የተከበበች በመሆኑዋ ልዪ ውበትን አጎናጽፏታል ፡፡

ኮሶየ በ1957 ዓ.ም በቀዳማዊ አፄ ሀይለ ስላሴና በወቅቱ የእንግሊዝ ንግስት በነበሩት በንግስት ኤልሳቤት መካከል ተመራጭ ቦታ ሆና በመገኘቷ የሁለቱን መንግስታት ውይይት አስተናግዳለች ፡፡

በዚህም በታሪክ ስትወሳ ትኖራለች እንግዲህ የጪጊ ማርያም ገዳምና የአባ ምዕመነ ድንግል ዋሻም የሚገኘው ከዚህች ቀበሌ ማዕከል ተነስተን ወደ ሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ ፊታችን በማዞር በእግር ለ3፡00 /ለሶስት ሰዓት/ የዛጎል አንባን ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችንና የጅብ ዋሻ አካባቢን አቋርጠን  ከተጓዝን በኃላ በጉንዳ ጩጊ ቀበሌ ውስጥ ይገኛሉ ፡፡ አንባውን ጨርሰን ወደ ምስራቅ ስንታጠፍ ደግሞ በተፈጥሮ ክብ ቅርፅ ያለውና ፍፁም ቤተ-ክርስቲያን መስሎ የሚታየውን ተራራ እናገኛለን ፡፡ በዚህ ተራራ ላይ አባ ምዕመነ ድንግል በ16ኛው መቶ ክፍል ዘመን የገዳም ህይወታቸውን እንዳሳለፉበት የሚነገር ሲሆን በአሁኑ ወቅት በገዳምነት እያገለገለ ይገኛል ፡፡ ወደ ተራራው ስንሄድ በቅድሚያ ለፀበልተኞች የተዘጋጀውን የቆርቆሮ መጠለያ ከዚያም ማይ ዪርዳኖስ ጸበልንና ዋሻ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ-ክርስቲያንን አእናገኛለን ፡፡ ቤተ-ክርስቲያኑ ቅስትና መቅደስ ያለው ሲሆን በቅድስቱ ማይዮርዳኖስ ጸበልን በመጠጣታቸው ስጋቸው ያልፈረሰ የፍየል አጽሞች ይገኛሉ ፡፡

 

የማይ ዮርዳኖስ ፀበል በክረምትም ሆነ በበጋ አንድ አይነት ይዘት ያለው ሲሆን ዓመቱን በሙሉ ቢቀዳ የውሃው መጠን የማይቀንስና የማይጨምር በምንም መንግድ ሌላ ውሃ ወደ ፀበሉ የማይገባ መሆኑ የበለጠ ታምር ያሰኛል ፡፡በዚህ ዋሻ በሚገኘው ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ በአመት አንድ ጊዜ ማለትም ጻጊሜ 03 ብቻ ይቀደስበታል ፡፡ በዕለቱም በዙ ምዕመናን የበዓሉ ተካፋይ ይሆናሉ ፡፡ ከቤተ-ክርስቲያኑ ወጥተን ጉዞዓችን ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ስናደርግ ደግሞ የአቡነ አረጋዊና የኪዳነምህረት ጸበልን እናገኛለን ፡፡ ይንን ሁሉ ከተመለከትን በኃላ ተመልሰን ወደ ጪጊ ማርያም ገዳም እንሄዳላን ፡፡ ገዳሙ የወንዶችና የሴቶች ተብሎ የተለየ ሲሆን በወንዶች ገዳም በኩል ይገኛል ፡፡ ወደ ሴቶች ገዳም ስናመራ ደግሞ አንድ ትልቅ የችብሃ ዛፍ ወድቆ እንደተነሳና ይሄውም በሰው ልጅ ሞቶ መነሳት ጋር የተያያዘና እግዚአብሄር ታምርን እንዳሳየበት ይነገራል  ዛፋ ከስራ አምስት አመት በኃላ ዞሮ እንደወደቀና በስሩ የፈለቀው ፀበልም በሽተኞችን እንደሚፈውስ አባቶች ይናገራሉ ፡፡ የጩጊ ማርያም የንግስና በዓል በየዓመቱ ሰኔ 21 ቀን ከተለያዪ የወስጥ ሀገር እና የውጭ ሀገር በሚመጡ ጎብኝዎች ተከብሮ ይውላል ፡፡

 
Horizontal SlideShow
Horizontal SlideShow Module v1.8 by JT.
Search
Who is Online
We have 1 guest online
What is your Opinion About This Site?